የአልጀሪያው አትሌቲክስ ልዑክ ሽልማት ተበረከተለት

ሰኔ 28፣2009

በ13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ትናንት ምሽት በአራራት ሆቴል ሽልማት ተበረከተለት፡፡

ፌደሬሽኑ ለሽልማቱ 850 ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡

በውድድሩ ወርቅ ሜዳሊያ ያመጡ አትሌቶች 17ሺህ ብር፣ ብር ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች 13ሺህ ብር እንዲሁም ነሐስ ላስገኙ አትሌቶች ደግሞ 9ሺህ 5 መቶ ብር ተሸልመዋል፡፡

ዲፕሎማ ላመጡ አትሌቶች 5ሺህ ብር እንዲሁም ለተሳተፉ አትሌቶች 2 ሺህ ብር ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ለቡድኑ አባላት የ500 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡

ኮሜቴው ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለሚደግፋቸው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክቶች ድጋፍ የሚውል 5 ሚሊየን ብር ሰጥቷል፡፡

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በማትታወቅባቸው የ4 መቶ እና 8 መቶ ሜትር ውድድሮች ወርቅ መገኘቱ እንደ መልካም ጅምር ታይቷል ተብሏል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ  ሃይሌ ገብረስላሴ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ13 ወርቅ፣ በ13 ብር፣ በ12 ነሃስ፣ በድምሩ በ38 ሜዳልያዎች ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች