የሻምፒዮናው ሻምፒዮና አዲስ አበባ ገባ

ሰኔ 27፤2009

በአልጀሪያ በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ሉዕካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ቡድኑ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳት ሻለቃ ሀይሌ ገብረ ስላሴን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች አቀባብል አድርገውለል፡፡

ቡድኑ ዛሬ ምሽት 12፡00 ሰዓት የማበረታቻ ሽልማት በአራራት ሆቴል እንደሚደረግለትም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በበላይነት መፈፀሟ በተተኪዎች  ተስፋ እንድታደርግ መሰረት ይጥላል ተብሏል፡፡

ቡድኑ 38 ሜዳሊያ በመሰብሰብ የውድድሩ ፈርጥ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ዘገባው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ነው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች