ጀርመን የፊፋ ኮንፈደሬሽን ካፕን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፈች

ሰኔ 26፤2009

በሩሲያ ሲደረግ የነበረው የፊፋ ኮንፌደሬሽን ካፕ በጀርመን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

ጀርመን ይህንን ዋንጫ ስታነሳ የመጀመሪያ ጊዜዋ ሲሆን የቺሊው ተከላካይ የፈጸመውን አጋጣሚ በመጠቀም በ20ኛው ደቂቃ ላርስ ስቲድል ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ነው የድል ባለቤት መሆን የቻለችው፡፡

ቺሊዎች በአሌክሲስ ሳንቼስ እና አርትሮ ቪዳል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም ኳስና መረብን ማገናኘት አልቻሉም፡፡ ቺሊ በጨዋታው አብላጫ ወስዳ ነበር፡፡

በዚህ ጨዋታ ላይ አጨቃጫቂ ክስተቶች የተፈጠሩ ሲሆን የቺሊው ተከላካይ የጀርመኑን ቲሞ ወርነርን በክርን ገጭቶ በቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ የተላፈበትና ውሳኔ ለማስተላለፍ የቪዲው ምልከታ ከአራት ደቂቃ በላይ መፍቱ ይጠቀሳል፡፡

የጀርመን ብሄራዊ ቡድን በአብዛኛው በወጣቶች የተገነባ ሲሆን ሀገሪቱ ወደ ፊት ጥሩ ተስፋ እንደሰጣት እየተነገረ ነው፡፡

ለደረጃ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ፖርቹጋልና ሜክሲኮ በመደበኛውና በጭማሪው ሰዓት አንድ አቻ በሆነ ውጤት በማጠናቀቃቸው በተሰጠው መለያ ምት ፖርቹጋል 2ለ1 ማሸነፍ ችላለ፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች