ቺሊ ለኮንፈደሬሽን ካፕ ፍጻሜ ደረሰች

ሰኔ 22፤2009

በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የኮንፈደሬሽን ካፕ ጨዋታ ቺሊ ፖርቹጋልን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛው ሰዓት ያለምንም ግብ ዜሮ ለዜሮ በማጠናቀቃቸው በተጨመረው ሰዓትም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡

በመሆኑም ሁለቱን ቡድኖች ለመለየት በተሰጠው መለያ ምት ቺሊ 3 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረስ ችላለች፡፡

በጨዋታው ቺሊ የጨዋታ የበላይነት የነበራት ሲሆን በተለይ አርትሮ ቪዳልና አሌክሲስ ሳንቼስ ያመከኗቸው እድሎች የሚያስቆጩ ነበር፡፡

በቺሊ በኩል አሌክሲስ ሳንቼስ በፖርቹጋል በኩል ደግሞ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ፉክክር ተጠባቂ ነበር፡፡

ዛሬ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት የጀርመንና ሜክሲኮ አሸናፊ ከቺሊ ጋር ለዋንጫው ይፋለማሉ፡፡

ከዚህ ጨዋታ በኋላ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የደረጃ ጨዋታ ላይ ሳይሳተፍ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ የልጅ አባት በመሆኑ ባለቤቱንና ልጁን ለመጎብኘት ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ ፊፋ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች