የዘንድሮው የወንዶች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይፈጸማል

ሰኔ 16፤2009

የዘንድሮው የወንዶች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ በአዲስ አበባ እና በክልሎች ከተሞች በተመሰሳይ 9 ሰዓት በሚደመሩ ጨዋታዎች ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ፡፡

በ30ኛው ሳምንት በሚደረጉ ጨዋታዎች በቀጣዩ ዓመት ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡት ክለቦች እንዲሁም በፕሪምየር ሊጉ የሚቆዩት ክለቡች ይለዩበታል ፡፡

ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከጅማ አባ ቡና፣ ሶደ ላይ ወላይታ ዲቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ሰበታ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ ፣ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዩርጊስ ዋንጫ በሚያነሳበት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም በወራጅ ቀጠና ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናግዳል፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከመከላከያ እና አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከፋሲል ከተማ ጋር ይገናኛሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች