በኮንፈደሬሽን ካፕ የምድብ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

ሰኔ 16፤2009

ትላንት ምሽት በተካሄደው የፊፋ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታ ቼሊ ከጀርመን አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በጨዋታው የአርሴናሉ አሌክሲስ ሳንቼዝ ሀገሩን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ማስቀጠር የቻለ ሲሆን ይህቺ ግብም ለሀገሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች 38 በማድረስ የቺሊ የምንጊዜም የጎል አስቆጣሪነቱን ክብረ ወሰን ተርክቧል፡

ጨዋታው በተጀመረ በ6ኛው ደቂቃ ላይ ጀርመናው ኢንተርናሽናልና የአርሴናሉ ተከላይ ሙስጠፋ ስህተት የተገኘውን አጋጣሚ የቡድኑ አምበል ሳንቼዝ ወደ ጎል መቀየር ችሏል፡፡ 

ለጀርመን ላርስ ስቲነድል በ61ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ቺሊ ምድብ በሁለት ጎል ክፍያ ጀርመንን በልጣ መምራት ችላለች፡፡

ቺሊ እና ጀርመን ወደ ቀጣዩ  ዙር ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡

በምድብ ሁለት የተደረገው ሌላኛው ጨዋታ አውስትራሊያ ካሜሮን በተመሳሳይ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ካሜሮን በጨዋታው ቀዳሚ የሆነችበት ጎል በ45ኛው ደቂቃ አንጉሳ አማካኝነት ስታገኝ አውስትራሊያ በ60ኛው ደቂቃ ባገኘችው የፍጹም ቅጣት ምት  ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

አውስትራሊያና ካሜሮን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የግድ የጀርመንና የቺሊን በሰፊ የጎል ልዩነት መሸነፍ ይጠብቃሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች