ደደቢት በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል በጥሎ ማለፉ ድል ቀንቷቸዋል

ሰኔ 14፤2009

ዛሬ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ደደቢት ሲዳማ ቡናን 1 ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

የመጀመሪያው አጋማሽ 0ለ0 በሆነ ውጤት ያጠናቀቁት ሁለቱ ቡድኖች ከእረፍት መልስ ጌታነህ ከበደ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ደደቢት ሙሉ 3 ነጥብ ማግኘት ችላል፡፡፡

በዚህም ደደቢት ነጥቡን 48 በማድረስ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን ያስተናገደበት ሲሆን ፋሲል ከነማ በፍጹም ቅጣት ምት መለያ 3ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታ አቤል ያለው ፋሲል ከነማን በ27 ደቂቃ መሪ ያደረገ ጎል ሲያስቆጥር  ቡልቻ ሹራ እና ዳዋ ሁቴሳ ባስቆጠሩት ጎል አዳማን መሪ  ማድረግ ችለው ነበር፡፡

ይሁንና ፋሲል ከነማዎች በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ ኤርሚያስ ኃይሉ ባስቆጠራት ግብ መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ2 አቻ ውጤት ተጠናቋል፡

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያት ምት ፋሲል ከነማ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አዳማ ማሸነፍ ችሏል፡፡

ምንጭ፡ ኢትዮላይቭስኮር/ሶከርኢትዮጵያ
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች