በኮንፈደሬሽን ካፕ ሩሲያ ከፖርቹጋል የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል

ሰኔ 14፤2009

በሩሲያ አስተናጋጅነት እየተደረገ ባለው የፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ይውላል፡፡

በዚህም አስተናጋጇ ሩሲያ ከፖርቹጋል እንዲሁም ሜክሲኮ ከኒውዜላንድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የመጀመሪያውን ጨዋታን በድል የጀመረችው ሩሲያ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከአውሮፓ አሸናፊዋ ፖርቹጋል ጋር ታደርጋለች፡፡

ፖርቹጋል የመጀመሪያዋን ጨዋታ በአቻ ውጤት ነበር ያጠናቀቀችው፡፡

ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት የሰጠችው ሩሲያ በሜዳዋ እና በደጋፊዋ ፊት እንደመጫወቷ ጨዋታውን እንደምታሸንፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቷታል፡፡

ከሰሞኑ በስፔን መንግስት ክስ የቀረበበት የዓለማችን ቁጥር አንድ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሙሉ ትኩረቱን ለጨዋታው እንዳደረገ  አሰልጣኙ ፈርናንዶ ሳንቶስ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ የኦሽኒያ አሸናፊዋ ኒውዜላንድ ከኮንካ ካፕ አሸናፊዋ ሜክሲኮ ጋር ይትጫወታለች፡፡ ሜክሲኮ የመጀመሪያው ጨዋታ በአቻ ውጤት ስታጠናቅቅ ኒውዜላንድ በሩሲያ ሽንፈትን ቀምሳለች፡፡

ነገ ቀጥሎ በምድብ ሁለት ካሜሮን ከአውስትራሊያ ጀርመን ከቺሊ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች