ቅዱስ ጊዩርጊስ በተከታታይ ለ4ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አሸነፈ

ግንቦት 11፣2009

በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 በማሸነፍ ለአራት ተከታታይ አመታት አሸናፊ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ባደረገው ጨዋታ 1 ለ ባዶ በማሸነፍ ነው ለ4ኛ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው፡፡

ቅዱስ ጊዩርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለአራት ተከታታይ አመታት በማንሳት  አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ  አዳነ ግርማ  በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ግብ ጊዩርጊስን ለአዲስ ክብር አብቅቷል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ጨዋታዎች 55 ነጥብ በመሰብሰብ ነው ሻምፒዮን መሆኑ ያረጋገጠው  ደደቢትና ሲዳማ በእኩል 48 ነጥብ  በጎል ክፍያ ተበላልጠው እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በሌላ ጨዋታ ደደቢት ወደ አዳማ ተጉዞ በአዳማ ከተማ 2ለ1 በሆነ ውጤት በመሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነት እድሉ አምክኗል።

ፋሲል ከነማ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በፋሲል ከነማ  3 ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ወልዲያ ከነማ ከጅማ አባቡና፣ ሲዳማ ቡና ከአርባ ምንጭ ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡

ድሬዳዋ ከነማ ሀዋሳ ከነማን እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ወላይታ ድቻን በተመሳሳይ  1 ለ 0 መርታት ችለዋል።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች