ደደቢት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

ግንቦት 7, 52009

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ትናንት ፍፃሜውን ሲያገኝ ደደቢት ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ የሀዋሳ ከተማ ከ17 አመት በታች ቡድን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ17 በታች ዋንጫን አንስቷል፡፡

ደደቢት ተጋጣሚውን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 0 አሸንፎ ነው የዋንጫ ባለቤት የሆነው፡፡

አዳማ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ለደረጃ ተገናኝተው አዳማ በተመሳሳይ 2 ለ 0 ረቶ ዓመቱን ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ተሸናፊው ሀዋሳ ከተማ 4ኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድል ያልቀናው ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመለያ ምት በመርታት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አንስቷል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ሙሉ የጨዋታ ጊዜአቸውን 1 ለ 1 በማጠናቀቃቸው ነው ወደ መለያ ምት ያቀኑት፡፡ በዚህም ሀዋሳ 4 ለ 2 ረቷል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች