ሊቨርፑል የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን በራሱ የሚወስንበትን ውጤት አግኝቷል

ግንቦት 06፣2009

ዛሬ በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወደ ለንደን ያቀናው ሊቨርፑል ዌስትሃምን 4 ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

በውጤቱም ሊቨርፑል የሶስተኛ ደረጃውን አስጠብቆ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳፊነቱን በራሱ የሚወስንበትን ውጤት ይዞ ተመልሶል፡፡ በጨዋታው በ35 ደቂቃ ዳንኤል እስተሪጅ ከጥር ወዲህ የመጀመሪያ ጎሉ ለሊቨርፑል አስቆጥሮ የመጀመሪያ አጋማሽ በ ሊቨርፑል መሪነት ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ብራዚላዊው ፊሊፕ ኮቲኒዮ ሁለት ጎሎችና በኦሪጊ አንድ ጎል ሊቨርፑል 4 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

በቀጣይ በሚደረገው የመጨረሻ የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ ሊቨርፑል ከሚዲልስቦሮ ጋር በድል ካጠናቀቀ ለሚቀጥለው የውድድር ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋግጣል፡፡

በሌላ ጨዋታ የዋንጫ ተፎካካሪ የነበረው ቶተንሃም በሜዳው ማንችስተር ዩናይትድን አስተናግዶ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቶተንሃም ጨዋታው በተጀመረ በ6ኛው ደቂቃ በዋንያማ ጎል መሪ መሆን ችሏል፡፡ ከዕረፍት መልስ በ48ኛው ደቂቃ በውድድር ዓመቱ ምርጥ አቋም ላይ የሚገኘው ሀሪ ኬን በውድድር ዓመቱ በአጠቃላይ ጨዋታዎች 28ኛውን ጎል ማቆጠር ችሏል፡፡ ለዩናይትድ ሩኒ በ71 ደቂቃ ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች