ቅዱስ ጊዮርጊስ ከማማሎዲ ሰንዳውንስ ጋር አቻ ተለያየ

ግንቦት5 / 2009

ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቆ ከሜዳው ውጭ አንድ ነጥብ አስመዘገበ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምናው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ነው 0 ለ 0 የተለያየው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ እና ተከላካዮቹ የደቡብ አፍሪካውን ክለብ የማጥቃት እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ጨዋታው ያለምንም ግብ ለእረፍት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል፡፡

ፈረሰኞቹ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻሉ ቢሆንም በሰንዳውንስ የግብ ክልል ውጤታማ መሆን አለመቻላቸው ጎል እንዳይስቆጥሩ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ ከሜዳው ውጭ አስመዝግቦ ተመልሷል፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት የቱኒዝያው ኤስፔራንስና ቪታ ክለብ ጨዋታቸውን ትላንት አካሂደዋል፡፡

በዚህም ጨዋታውን በሜዳው ያደረገው ኤስፔራንስ 3 ለ 1 አሸናፊ ሆኗል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች