ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የአምናውን ሻምፒዮን ይገጥማል

ግንቦት 4፣2009

በምድብ ሶስት የሚገኘው ቅዱስ ጊዩርጊስ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ  የመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከደቡብ አፍሪካው ማሚሎዲ ሰንዳውን ጋር እሁድ በፕሪቶሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በጨዋታ መደራረብ ብንደክም ክብራችውን ለማስጠበቅ እንጫወታለን ያሉት  የሰንዳውን አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲሞኒ "የቅዱስ ጊዩርጊስ ተጫዋቾች እንደኛ ጫና አልተፈጠረባቸውም ተዝናንተው እንቅስቃሴያችንን እየተመለከቱ ነው" በማለት አስተያየታቸውን ሰተዋል፡፡

ስንዳው የ2016 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የግብጹን ዛማሊክን በድምር ውጤት 3ለ1 በማሸነፍ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

ቅዱስ ጊዩርጊስ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ የገባ የመጀመሪያ የኢትዮፕያ ክለብ ሲሆን ፣4ቱንም የማጣሪያ ጨዋታ ማሸነፍ ችለዋል፡፡

የቡድኑ አጥቂ ሳላሃዲን ሰዓዲ ደግሞ በአምስት ቻምፒዮንስ ሊግ ጎሎን የከፍተኛ ጎል አግቢነት እየመራ ይገኛል፡፡ 

ቅዱስ ጊዮርጊስ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከ10 ቀናት በኋላ ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ ክለብ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች