ማንችስተር ዩናይትድ በዩሮፓ ሊግ ለፍጻሜ መድረሱን አረጋገጠ

ግንቦት 4፣2009

ትናንትና ምሽት በሜዳው የስፔኑን ሴልታቪጎ ያሰተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በ17 ደቂቃ ማርዋን ፌላኒ ከራሽፎርድ የደረሰው ኳስ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠረው ጎል ዩናይትድን ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ተስፋ የሰጠች ሆናለች፡፡

ሴልታቪጎ በጨዋታ መጠናቀቂያ  በፋኩንዶ ሮካሊጋ ጎል ጨዋታውን አጓጊ ያደረገ እንዲሆን ቢያደርገውም ሴልታቪጎዎችን ከመውደቅ አላገዳቸውም፡፡ የስፔኑ ክለብ ለማለፍ ተጨማሪ አንድ ጎል ያስፈልገው ነበር፡፡

በጨዋታው የዩናይትዱ ኤሪክ ቤሊ እና የሴልታቪጎ ፋኩንዶ ሮካሊጋ ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብተዋል፡፡ ጨዋታውም አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ዩናይትድ በድምር ውጤት 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ለፍጻሜ በማለፍ ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ለመመለስ ተስፋ ሰንቀዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ የሆላንዱን አያክስ በሜዳው ያስተናገደው ኦሎምፒክ ሊዮን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም በድምር ውጤት አያክስ 5ለ4 ማሸነፍ በመቻሉ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

የፍጻሜውም ጨዋታ ግንቦት 16/2009 በስዊድን ስቶኮም ዩናይትድ ከ አያክስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች