ጁቬንቱስ ለካርዲፉ ፍፃሜ ደረሰ

ግንቦት 2፣ 2009

በምሽቱ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሞናኮን 2ለ1 የረታው ጁቬንቱስ በሶስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለፍፃሜ ደረሷል፡፡

ጁቬንቱስ በድርሶ መልስ 4ለ1 ነው ሞናኮን ማሸነፍ የቻለው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ከሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ አሸናፊ ይጋጥማል፡፡

ለጁቬንቱስ የምሽቱን የአሸናፊነት ግቦች በማዙኪች እና አልቬስ አማካኝነት አግኝቷል፡፡ ማፔ ለሞናኮ ማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ጁቬንቱስ ከሜዳው ውጭ 2ለ0 አሸንፎ የተመለሰ በመሆኑ በሜዳው ያደረገውን ጨዋታ ያለ ከፍተኛ ስጋት አድርጓል፡፡

ጁቬንቱስ እ.አ.አ በ2015 በሻምፒዮንስ ሊጉ ከባርሲሎና ጋር ለፍፃሜ ደርሶ መሸነፉ ይታወሳል፡፡በዚህ ዓመትም ከስፔን ክለቦች አንዱን ማገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

ተጋጣሚውን ለመለየትም የሪያል ማድሪድ እና የአትሌቲኮ ማድሪድ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡ ሪ.ማድሪድ በመጀመሪያው ጨዋታ 3ለ0 መርታቱ ይታወሳል፡፡

ጁቬንቱስ እ.አ.አ በ1996 አያክስን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፎ የዋንጫ መብላቱ ይታወሳል፡፡

የፍፃሜው ጨዋታ በዌልስ ካርዲፍ ስታዲዮም ይደረጋል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች