በሻምፒዮን ሊጉ የመልስ ጨዋታ ሞናኮና ጁፕቬንቱስ ዛሬ ምሽት ይገናኛሉ

  ግንቦት 01፣ 2009

በዛሬው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ጁፕቬንቱስ በሜዳው ሞናኮን  ያስተናግዳል።

ሁለቱ   ክለቦች በአውሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ተገናኝተው  ጁቬንቱስ ሞናኮን በሜዳው ሁለት ለባዶ  አሸንፎት ነበር የተመለሰው።

ሞናኮዎች ለዋንጫ ለመድረስ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ የተቆጠሩባቸውን ሁለት ግቦች  ለማካካስና  ብልጫ  ይዞ  ለመውጣት ሲሉ  ከጁቬንቱስ ጋር ዛሬ ምሽት 4:45 ላይ ከባድ ትንቅንቅ ያደርጋሉ   ተብሎ  ተጠብቋል።

በአንፃሩ ቀድሞ  በድል የተመለሰው  ጁቬንቱስ በጠንካራ  የተከላከይ መስመሮቹ   ጭምር በቀላሉ ለሞናኮ ይበገራል ተብሎ  አይታሰብም።

የፈረንሳዩ  ክለብ ሞናኮ ዛሬ የሚሸነፍ ከሆነ ጉዞው የሚገታ ሲሆን  በአንፃሩ  የጣሊያኑ   ጁቬንቱስ ድሉን  አስጠብቆ ከወጣ በነገው  ዕለት የመልስ ጨዋታ ከሚፋጠጡት ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ ማድሪድ አሸናፊ  ጋር ለዋንጫ  የሚደርስ ይሆናል።

ሪያልማድሪድ በመጀመሪያው ዙር የሻምፒዮን ሊጉ  ጨዋታ በሮናልዶ  ሶስታ  ግቦች አትሌቲኮ ማድሪድን በባዶ  መርታቱ  ይታወሳል።         

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች