ቅዱስ ጊዮርጊስ በማሸነፍ ለዋንጫ ያለውን ተስፋ አለመለመ

ሚያዝያ 29፣ 2009

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ በማሸነፍ ለዋንጫ ያለውን ተስፋ አለምልሟል፡፡

በሜዳው የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናገደው ጅማ አባቡና ተሸንፏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዕረፍት መልስ በ56ኛው ደቂቃ ሳልሃዲን ሰኢድ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፎ ለዋንጫ ያለውን ተስፋ አለምልሟል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደደቢትና ፋሲል ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ባለሜዳው ደደቢት አሸናፊ ሆኗል፡፡

ደደቢት 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ጎሎቹን ጌታነህ ከበደ በ41ኛው እና በ78ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ፋሲል ከተማ ብቸኛዋን ጎል በኤዶም ኮድዞ አስቆጥሯል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ሁለተኛ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡናና በኢትዮ-ኤሌክትሪክ መካከል ነበር፡፡ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ተክሉ ተስፋዬ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ቀዳሚ ሲያደርግ ኢትዮጵያ ቡና በሳሙኤል ሳኑሚ አቻ መሆን ችሏል፡፡

ሃዋሳ ላይ በተደረገ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ወልዲያን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ፍሬው ሰለሞንና ጃኮ አረፋት ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሃዋሳ የመራ ሲሆን ወልዲያን ከሽንፈት ያላዳነች ጎል አንዱአለም ንጉሴ ከመረብ አሳርፏል፡

አርባምንጭ ላይ የተካሄደው የአርባ ምንጭ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ጎል አቻ ተጠናቋል፡፡

ትላንት በተካሄዱ የሊጉ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዋች መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል፡፡

መከላከያ 1 ለ 0 ድሬዳዋን ሲያሸንፍ ብቸኛዋን ጎል ባዬ ገዛኸኝ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ጋብሬል አህመድ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ሙሉ ዓለም መስፍን ለሲዳማ ቡና ባስቆጠሯቸው ጎሎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያተዋል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ነገም ሲቀጠል አዲስ አበባ ከተማ ወላይታ ዲቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገጥማል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች