ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የፕራግ ማራቶንን በበላይነት አጠናቀቁ

ሚያዝያ 29፣ 2009

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የፕራግ ማራቶንን በበላይነት አጠናቀቁ፡፡

በወንዶች ምድብ በተደረገ ውድድር ኢትጵያዊያን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ቦታ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ገብረጻድቅ አብርሃ ውድድሩን 2፤08፤47 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ለመሆን ችሏል፡፡

ባዙ ወርቁና መኩዋንት አየነው ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ምድብ በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

ኬንያዊቷ ቫላሪ ጀሚሊ አይአቤይ 2፡21፡57 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች፡፡

አማኔ በሪሶ በ2፣22፣15 ሁለተኛ ስትሆን ታደለች በቀለ በ2፡22፡23 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች፡፡

ፈይሴ ታደሰ አምስተኛ ሰስተወጣ ሙሉ ሰቦቃ ሰባተኛ ሆናለች፡፡

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች