ጁቬንቱስ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሜዳው ያለመሸነፍ ክብሩን አሰጠበቀ

ሚያዝያ 04፣2009

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሜዳው ባርሲሎናን ያስተናገደው ጁቬንቱስ 3ለ0 በመርታት በሜዳው ያለመሸነፍ ክብሩን አስቀጥሏል፡፡

ጁቬንቱስ እስካሁን በ21 የአውሮፓ መድርክ ጨዋታዎች በሜዳው ሽንፈት አልቀመሰም፡፡

በዶርቱመንድ ተጨዋቾች መኪና ላይ በደረሰው ፍንዳታ ሌላውን የዕለቱ መርሃ ግብር አስትጓጉሏል፡፡

ለጁቬንቱስ የድል ግቦችን ዲባላ በመጀመሪያው ግማሽ ሁለት እንዲሁም ችሊኒ በሁለተኛው ግማሽ ሶስተኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው ጁቬንቱስ የባርሲሎናን እንቅስቃሴ ለመግታት ስልታዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አምሽቷል፡፡ ባርሲሎናዎች  አልፎ አልፎ የፈጠሯቸውን የግብ ዕድሎች አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቡፎን አምክኖባቸዋል፡፡

በጨዋታው ጁቬንቱስ 68 በመቶ የኳሰ ቁጥጥር ብልጫ ወስዷል፡፡ዲባላ የጨዋታው ኮከብም ተብሏል፡፡

ሁለቱ ግቦች የእኛ ስህተቶች ነበሩ፣ ቢሆንም በመልሱ ጨዋታ የሚቻለውን እናደርጋለን  የባርሲሎናው አሰልጣኝ ሊዊስ ኢንሪኬ አስተያይቱን ሰጥቷል፡፡

ማሲሚላሮ አሌግሪ በበኩላቸው ቡድኔ ትልቅ ስራ ስርቷል፣ ነገር ግን ስራችን አላለቀም ፒኤስ ጂ ዎች  አራት ግብ በሜዳቸው አስቆጥረው በመልሱ  ምን እንደገጠማቸው እናውቃለን ብለዋል፡፡

ትናንት ሊደረግ ታስቦ የነበረው የዶርቱመንድ እና የሞናኮ ጨዋታ በዶርቱመንድ አውቶቢስ ላይ በደረስው ፍንዳታ ምክንያት ለዛሬ ተላልፏል፡፡ ፍንዳታው በዶርቱመንድ ተከላካይ ባርትራ  ላይ ጉዳት ማድረሱ ተዘግቧል፡፡

በፍንዳታው የዶርቱመንድ ተጨዋቾች ከፍትኛ ድንጋጤ እንደተሰማቸው ተገልጿል፡፡ የፊፋ እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንቶች  ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 2፡45 ሊደረግ ቀነ ቀጠሮ ትይዟል፡፡

አትሌቲኮ ማድሪድ ከሌሲስተ፣ ባየር ሙኒክ ከሪያል ማድሪድ የዛሬ የሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብሮች ናቸው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች