ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሆኑ

መጋቢት 25፣2009

ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለቀጣዮቹ አራት አመታት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴን ለመምራት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

ኮሜቴው መጋቢት 23 መደበኛ ስብሰባውን አድርጓል፡፡

ጉባኤው ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ቦርድ መርጧል፡፡

አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ በቀለ ፣ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ ወይዘሮ ሔሮዳዊት ዘለቀ ፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ፣ ዶክተር ዳዲ ወዳጆ ፣ አቶ ዳዊት አስፋው፣ እንዲሁም አቶ ኪሮስ ሀብቴ የቦርዱ አባላት ሆነው የተመረጡ ናቸው።

አዲሱ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ስልጣናቸውን የተረከቡት ከአቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ያሉት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንን በፕሬዝዳንትነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ኦሎምፒክ ኮሚቴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች