ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ሙሉ አቅም አላት፡-አቶ ደመቀ መኮንን

መጋቢት 6፡2009

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ሙሉ አቅም እንዳላት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

ዛሬ በተጀመረው 39ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና የ60ኛው የካፍ ምሥረታ በዓል ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ መንግስት በአሁኑ ወቅት ለስፖርቱ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው በዚህም የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ)ና ካፍ መስፈርትን የሚያሟሉ አራት ትላልቅ ስቴዲየሞች ገንብቷል ብለዋል።

መንግስት ከሚገነባቸው ስቴዲየሞች በተጨማሪ በባለሀብቱ ሺህ መሀሙድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ወጪ በወልዲያ ከተማ ጥራቱን የጠበቀ ስታዲየም ተገንብቶ መመረቁንም ተናግረዋል።

"የአህጉሪቷ ስፖርት በተለይም እግር ኳስ ማደግ የሚችለው  ከፊፋና ከካፍ በሚሰጠው ድጋፍ አይደለም" ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለስፖርቱ ዕድገት ዋና መሰረት ህብረተሰቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

በጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ የካፍ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሀያቱ፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚንስትር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎችም አንጋፋ ተጫዋቾችና የካፍ ስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች