በኤፍኤው ካፕ ቼልሲ ዩናይትድን ጥሎ አለፈ

መጋቢት 05፣2009

ትናንት ምሽት በስታንፎርድ ብሪጅ በተደረገው የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን በማለ1 ለ 0 በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ፡፡

የቸልሲን የማሸነፊያ ግብ ኮንቴ በሁለተኛው ግማሽ መጀመሪያ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ለግቧ መቆጠር የግብ ጠባቂው ዲያ አቋቋም አስተዋፅኦ ነበረው፡፡

ዩናይትድ በኳስ ቁጥጥር እና በግብ ሙከራ በተጋጣሚው ተበልጦ አምሽቷል፡፡

ዩናይትድ በ35ኛው ደቂቃ ሄሬራን በሁለት ቢጫ ካርድ ማጣቱ ውጤቱን የከፋ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ዩናይትድ የዓመቱን ዝቅተኛ የኳስ ቁጥጥር አስመዝግቧል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ የቸልሲው አሰልጣኝ አቶኒዮ ኮንቴ ሞሪኒሆን ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉበትን ድል አግኝተዋል፡፡

የተጫወትነው ከጥሩ ቡድን ጋር ነው፤ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋችን አስደስቶኛል ሲሉ የቸልሲው ዋና አሰልጣኝ ገልፀዋል፡፡

ስለ ቀይ ካርዱ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፣ ጨዋታውን ያየ የራሱን አስተሳሰብ ማራመድ ይችላልም ብለዋል፡፡

አሸናፊው  ቸልሲ ወደ ዋንጫው ለማምራት ቶተንሃምን ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች