ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን እሁድ ላለበት የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ኮንጎ አመራ

መጋቢት 01 ፣ 2009

በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ  ወደ አንደኛው ዙር የተሸጋገረው ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን እሁድ መጋቢት 3/2009 ዓ.ም ከኮንጎው ኤሲ ሊዩፓርድስ ጋር ላለበት ጨዋታ ወደ ኮንጎ አመራ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደዚህ ዙር  የተሸጋገረው ከ2 ሳምንት በፊ የሲሼልሱን ኮትዲኦር በድምር ውጤት 5 ለ 0 በመርታቱ ነው፡፡

 ክለቡ ከሊዮፓርድስ ጋር ያበትን ጨዋታ በድል ከተወጣ የመጨረሻ 16 ክለቦችን በመቀላቀል ወደ ምድብ ማጣሪያው የሚያልፍ ይሆናል፡፡

 ወደ ኮንጎ በተጓዘው ቡድን ውስጥ 18 ተጨዋቾች ተካተዋል፡፡

ምንጭ ፤ ኢቢሲ ስፖርት

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች