አርሴናል በታሪኩ ከባዱን የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት አስተናገደ

የካቲት 29 ፣ 2009

በሻምፒዮን ሊጉ የመልስ ጨዋታውን በኢምሬትስ ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረገው አርሴናል 5ለ1 ዳግም ተሸንፏል፡፡

አርሴናል በደርሶ መልስ 10ለ2 ሽንፈት በማስተናገዱም በታሪኩ ከባዱን የአውሮፓ መድረክ ሽንፈቱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ አርሴናል በዋልኮት የ20ኛው ደቂቃ ግሩም ግብ ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር ፡፡ ነገር ግን የአርሴናሉ ተከላካይ ኮሸልኒ በ54ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ ሎዋንዶንስኪ/ፍፁም ቅጣት ምት/፣ ሮበን እና ዳግላስ ኮስታ አንድ አንድ ግቦችን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

እንዲሁም ቪዳል  ሁለት ግቦችን ከመረብ ከመረብ በማሳረፍ የአርሰናልን መረብ አዳክመውታል፡፡ቪዳል የጨዋታው ኮከብ ሆኖም አምሽቷል፡፡

አርሴናል ባለፉት 7 ዓመታት ለተከታታይ 7 ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ 16 ቡድኖችን የተቀላቀለ ቢሆንም አንዱንም ጥሎ ማለፍ አልቻለም፡፡ በዚህ ዓመት የተቆጠረበት 10 ግብ ደግሞ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በመሆኑም በአርሴናል ቤት  ወንበር የሚያነቃንቁ  አስተያየቶች እየተደመጡ ይገኛል፡፡

ዘ ኤክስፕረስ የተሰኘው ጋዜጣ ዳግም ሀፍረት በሚል የቬንገርን ፎቶ ይዞ ወጥቷል፡፡ አይ ስፖርት የተባለው ጋዜጣ ደግሞ ቬንገር ይውጡ በሚል ሰፊ ፁሁፍ ይዞ ወጥቷል፡፡

ታይምስ ጋዜጣ  በተመሳሳይ ቬንገር በታሪክ አሳፋሪውን ውጤት አስመዘገቡ በሚል ፁሁፍ ደጋፊዎችን መስማት አስፈላጊ ነው በሚል ይዞ ቀርቧል፡፡

ሚረር ስፖርት ደግሞ ሳንቸዝ በተቀያሪ ወንበር ተቀምጦ ሲስቅ የሚያሳይ ፎቶ በመያዝ የአርስናልን ሽንፈት በስላቅ አሳይቷል፡፡

በጨዋታው የአርሰናል ደጋፊዎችም የመፀዳጃ ወረቀቶችን ወደ ሜዳ በመወርወር ጨዋታውን ሲያቋርጡ ታይቷል፡፡

በሌላ ጨዋታ ወደ ጣሊያን ተጉዞ ናፖሊን የገጠመው ሪያል ማድሪድ 3ለ1 አሸንፏ፡፡ በድምርም 6ለ2 በመርታት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች