አሰልጣኙን ያሰናበተው ሊስተር ሊቨርፑልን አሸነፈ

http://www.ebc.et/newstheme-theme/images/spacer.pngየካቲት 21፣ 2009

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት ያደረገውን አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪን ያሰናበተው ሌስተር ሲቲ በሜዳው ሊቨርፑልን አስተናግዶ 3ለ1 አሸንፏል፡፡

ሊስተር ወደ ሜዳ የገባው በተጠባባቂው አሰልጣኝ ክሬግ ሸክስፔር እየተመራ ነው፡፡

ለሌስተር ግቦችን ቫርዲ በ28ኛው እና በ60ኛው እንዲሁም ድሪክ ዋተር በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሊቨርፑል ከመሸነፍ ያልዳነበትን ግብ ኩቲኒዮ በ68ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው ሊቨርፑል የኳስ ቁጥጥር የበላይነት መውስድ ቢችልም አልተጠቀመበትም፡፡

ሌስተር ያሳየው አጨዋውት ባለፍው ዓመት ሻምፒዮን ሲሆን ካሳየው ጋር ተመሳሳይ ነው ተብሏል፡፡ በጨዋታው ሁለት ግቦችን ከመረብ ያገናኛው ቫርዲ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንዲዚህ ዓይነት ሽንፈቶችን ለመግለጽ ቃላት  መምረጥ ያስፈልጋል፣ ሌስተር ሀይል የተቀላቀለበት ጨዋታ ስለተጫወተ አይደለም ያሸነፈን እኛ ብቁ ስላልነበር እንጂ ሲሉ ጨዋታውን ገልጸውታል፡፡

ውጤቱ ሌስተርን ከወራጅ ቀጠና ያራቀ ሲሆን፣ ሊቨርፑል በአንጻሩ ከመሪዎቹ የተለያየበት  ሆኗል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች