ሌሲስተር የዋንጫ ባለቤት ያድረጉትን ክላውዲዮ ራኔሪን አሰናበተ

የካቲት 17፣ 2009

ሌስስተር የዋንጫ ባለቤት ያድረጉትን  አሰልጣኝ ክላውዲዮ  ራኔሪን አሰናበተ።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪኩ  ዋንጫ  አግኝቶ የማያውቀው   ሌሊስተር ሲቲ

ያለፈውን አመት ዋንጫ  እንዲያነሳ አሰልጣኝ ክልውዲዮ  ራኔሪ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል።

ክለቡ  በዚህም ከዋንጫ  ባሻገር ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነት እንዲበቃ  በማድረጋቸው ሙገሳ  ሲቸራቸው ቆይቷል።

በፊፋ  ደረጃም የዓመቱ  ምርጥ አሰልጣኝነትን አክሊል እስከ መድፋት ደርሰዋል።

ይሁንጂ  በተያዘው የሊጉ  የውድድር ዘመን ሌሲስተር አምና  ያስመዘገበውን ስኬት መድገም ሳይችል ቀርቶ በደረጃው ግርጌ  ላይ በመንደፋደፍ ላይ ይገኛል።በሻምፒዮንስ ሊጉ የጥሎ  ማለፍ የመጀመሪያ  ጨዋታ ሽንፈት ስለገጠማቸው፣  ሙገሳ ሲቸራቸው የነበሩት አሰልጣኝ ራኔሪ ትላትት ከክለባቸው ስንብት ገጥሟቸዋል።

የአሰልጣኙ  ስንብት ለብዙዎች የሚዋጥ አልሆነም።በድል ማግስት ገና ዘጠኝ ወር ሳይሞላቸው መባረራቸው አግባብ አይደለም፤ዕድል ሊሰታቸው ይገባ  ነበር የሚሉ  ሀሳቦች ተብራክተዋል ብሏል ቢቢሲ  በዘገባው ።    

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች