አቴሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፔን የ2ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት ሆነች

የካቲት 01 ፣2009

ገንዘቤ  ዲባባ በስፔን ሳባዴል  የ2ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን በማሻሻል አድስ ታሪክ አስመዝግባለች።

የሶስት ጊዜ  የቤት ውስጥ ሻምፒዮንና  የ1500 ሜትር ክብረ  ወሰን ባለቤት  የሆነችው አትሌት ገንዘቤ  ዲባባ የአውሮፓዊያኑ  2017 የውድድር ዘመኗን በአዲስ ክብረ  ወሰንና ድል ጀምራለች።

ትላንት በስፔን ሳባዴል በተካሄደው የቤት ውስጥ ውድድር እኤአ በ1998  በገብሬልሻ ሳዛቦ ተይዞ የነበረውን ምርጥ ሰዓት ገንዘቤ  በሰባት ሰከንድ በማሻሻል 5:23.75 በሆነ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች።

ገንዘቤ ያስመዘገበችው  ሰዓት ገና ይፋዊ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና  ሆኖ  ባይመዘገብም በርቀቱ  ከቤት ውስጥ ሻምፒዮና በተደረገ  ውድድር በሶኒያ ኦ ሱሊቫን ተይዞ  የነበረውን  ክብረ  ወሰን በሁለት ሰከንድ  በማሻሻሏ በክብረ  ወሰን ደረጃ  ሊመዘገብ የሚችል ሰዓት መሆኑን  የአለም አትሌቲክስ ማህበር ፌድሬሽን ዘገባ ያስረዳል።   

አትሌት ገንዘቤ ትላንት በስፔን ያስመዘገበችው ድል በቤት ውስጥ ሻምፒዮና ያስመዘገበችውን ድል ወደ ስድስትያሳድገዋል።

አትሌቷ ከዚህ በፊት በአንድ ማይል፣በሁለት ማይል፣በ1500ሜ፣ በ3000ሜ፣በ5000ሜ ጭምር የአለም ፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰን ባለቤትም ነች።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች