ካሜሮን ግብፅን በመርታት የአፍሪካ ዋንጫውን ለ5ተኛ ጊዜ አነሳች

ጥር 29፣ 2009

ካሜሮን ግብፅን በመርታት የአፍሪካ  ዋንጫውን ለ5ኛ  ጊዜ  አነሳች።

ላለፉት ሶስት  ሳምንታት በጋቦን ሊቨርቢሌ ሲካሄድ የሰበተው 31ኛው የጋቦኑ  አፍሪካ  ዋንጫ በካሜሮን አሸናፊነት ማሰረጊያውን  አግኝቷል።

ካሜሮን ግብፅን  2 ለ1 በመርታት ዋንጫውን ለመውሰድ አስራ አምስት አመታትን ለመጠበቅ ተገዳለች።

ካሜሮንና  ግብፅ  ትላንት ምሽት ባካሄዱት የዋንጫ ትንቅንቅ ግብፅ በሞሃመድ ኤልኔኒ በ22ኛው ደቂቃ ቀዳሚ  መሆን ብትችልም በአሸናፊነት መጨረስ የሚያስችላትን ውጤት ግን ይዛ  ሳትወጣ ቀርታለች።

ካሜሮን ካኃላ ተነስታ በሁለተኛው  አጋማሽ 59ኛው ደቂቃ ኒኮላስ  ኑኩሉ  አማካኝነት አቻ  መሆን ችላለች።   

ተቀይሮ  የገባው ሌላኛው ካሜሮናዊ  ቪንሰንት አቡበክር ደግሞ  ለካሜሮንም ሆነ ለራሱ በ88ኛው ደቂቃ  ታሪካዊ የተባለች ግብ ማስቆጠር በመቻሉ ባለድል ሆነዋል።

ካሜሮን የአፍሪካ  ዋንጫውን በመውሰድ ታሪክ ከግብፅ በመቀጠል ሁለተኛ መሆን ያስቻላትን  ውጤት ተቀዳጅታለች።

ካሜሮን ከግብፅ ጋር ለአፍሪካ  ዋንጫ ፍፃሜ  ሶስት ጊዜ ደርሳ ፈርኦኖቹን  አሸንፋ  ዋንጫውን ስትወስድ የአሁኑ የመጀመሪያዋ ነው።

ለዋንጫ  ይደርሳሉ  ተብለው ያልተገመቱት ካሜሮኖች ወሳኝ ተጨዋጮቻቸውን በጉዳት ሳያሰልፉ ጭምር በስተመጨረሻ ባለድል ሆነው ከሊቭርቢሌ ተመልሰዋል።

ግብፆቾ በተራቸው  ለስምንተኛ ጊዜ ዋንጫ ለመውሰድ  የነበራቸውን  ጉጉት ሳይሳካ በባዶ እጃቸው ለመመለስ ተገደዋል።

ግብፆች ቀደመው እየመሩ  በስተመጫረሻ  ዋጋ ለመክፈል ተገደዋል።ካሜሮኖች በምሽቱ ጨዋታ በጨዋታም ቢሆን የበላይ ሆነው ነበር ያመሹት።

ምንጭ ፥  ቢቢሲ    

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች