Back

የአለም ባንክ ለአፍሪካ የ57 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ

መጋቢት  11፣2009

የአለም ባንክ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለሚያካሂዱት የልማት ስራ የሚውል የ57 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ፡

ባንኩ ዛሬ መጋቢት 11፣2009 ይፋ ካደረገው የአጠቃላይ የድጋፍ ማዕቀፉ 45 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ ከአለም አቀፉ የልማት ማህበርና የአለም ባንክ ፈንድ ለአለም ድሃ አገራት ከሚሰጠው እርዳታና ከወለድ ነፃ ብድር የሚገኝ መሆኑን የአለም ባንክ ፐሬዝዳንት ጂም ዮንግ ኪም ተናግረዋል፡፡

ለግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲውል ደግሞ 8 ቢሊን ዶላር ተመድቧል፡፡ ከአህጉሪቱ አገራት ወደ መካከለኛ የምጣኔ ሀብት እድገት ውስጥ ለገቡ አገራት ባንኩ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል፡፡

የአለም ባንኩ ፕሬዝዳንት እንደሚሉት ባንኩ አሁን ያደረገው ድጋፍ የአህጉሪቱን ትምህርት፣ ጤና በንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በተቋማዊ ለውጥና በሌሎችም ጉዳዮች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ከአጋር አገራቱ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኪም ለዚሁ ድጋፍ አጋርነት ለማሳየት በትላንተናው ዕለት ወደ ታንዛያና ሩዋንዳ  ማቅናታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የቡድን 20 አባል አገራት ባለፈው አርብና ቅዳሜ ጉባኤያቸውን  በጀርመን ሲያካሂዱ ከአፍሪካ ጋር በቅርበት በመስራት ለእድገቷ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረጉ አስታወቀው ነበር፡፡


በኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የሚነሱ የሕዝብ ቅሬታዎችን ይፈታል የተባለ የሥራ መመሪያ ተዘጋጀ

የመቐለ ከተማ ወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ የሥራ ዕድል በማግኘታቸው ኑሮአቸው መሻሻሉን ገለፁ

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ት/ሚ ገለጸ

የአዳማና ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በያዝነው ወር መጨረሻ ይመረቃሉ

የኃይማኖት አባቶች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ

በአገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ኢህአዴግ የተመጣጣኝ ውክልና ድርሻ 15 በመቶ እንዲሆን ተደራደረ

በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ሲከሰት የነበረው ሁከት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ክልሉ አስታወቀ

መሬት ወስደው ባላለሙ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የጅማ ከተማ አስተዳደር ገለፀ

የህዳሴ ግድብ በስርአተ ትምህርት ውስጥ አካቶ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ