Back

የቻይናው አግዚን ባንክ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ260 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ

ግንቦት 11፣2009

የቻይናው አግዚን ባንክ በአዳማ ለሚገነባው የሁናን ኢንዱስትሪ ዞን የ260 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ።

ሰሞኑን በቻይና ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ግዛቶች ከኢትዮጵያ ጋር የንግድና የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ  ለማስቻል የሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም የታላላቅ ማሽነሪ አምራች የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች መገኛ በሆነችው ሁናን ግዛትም ተካሂዷል።

ፎረሙ  የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር ግብና የኢንቨስትመንት አቅም በማሳየት በኢትዮጵያ የተሻለ ተሳትፎ ያላቸው የሁናን ኩባንያዎች ኢንቨስትመንታቸው የበለጠ እንዲያጠናክሩ እድል የፈጠረ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከፎረሙ ባሻገር ከሁናን ግዛት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ኩባንያዎች ጋር የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስሩን ለማሳደግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ተወያዩተዋል።

በኢትዮጵያ መንግስትና በሁናን ግዛት የትብብር ግንኙነት አማካኝነት ለሚገነባው የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ  ፓርክ ግንባታ የቻይናው ኤግዚን ባንክ የሰጠው የ260 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነትም ተፈርሟል።

የአዳማ ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀይል ማመንጫዎችና ለታላልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚያገለግሉ ግዙፍ ትራንስፎርመሮችና ተያያዥ የኢንዱስትሪ  ውጤቶች ያመርታል።

ሪፖርተር:-አብዲ ከማል


በጅማ በሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተይዞ የቆየ መሬት ለ380 ለአከባቢው ወጣቶች ተሰጠ

ኢትዮጵያ አቶ ነዋየ ክርስቶስ ገብረአብን ለአፍሪካ ሕብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነርነት በእጩነት አቀረበች

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ኢትዮጵያና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የአማራ ክልል አርሶ አደሮች የማዳበሪያ ዋጋ ከአቅርቦቱ ጋር እንዳልተመጣጠነላቸው ገለጹ

29ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል

የወንዶገነት የደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ያሰለጠናቸው 338 ተማሪዎችን አስመርቋል

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በአስተዳደር ስርዓት ግንባታ ላይ ተባብረው ለመስራት ተስማሙ

የእስልምና እምነት ተከታዮች በሀገሪቱ እድገት ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ነው- ከንቲባ ድሪባ ኩማ