Back

ኢትዮጵያና አሜሪካ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የትብብር ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

ህዳር 28፣2010

ኢትዮጵያና አሜሪካ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የትብብር ግንኙነት  ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማማቶ ከተመራ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር በሁለትዮሽ  በአካባቢያዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋር የሆነችው አሜሪካ የምታደርገው ድጋፍ እንዲጠናከር  በሚያስችሉና በተለያዩ  መስኮች የስትራቴጂያዊ አጋርነት ግንኙነታቸውን በሚያጎለብቱ ጭብጦች  ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል..

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና የዴሊቨሪ  ዩኒት ሃላፊ አቶ ዛድግ አብረሃ ውይይቱ በ3 አብይ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደርና የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሩ ዶናልድ ያማማቶም ኢትዮጵያ የሀገራቸው ዋንኛ አጋር እንደሆነች ገልጸዋል፡፡

 

 

 


የአፍሪካ ሃገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ ለቴክኖሎጂ ልማት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል - ክርስቲን ላጋርድ

ተርኪሽ ኢንደስትሪ ሆልዲንግ በኢትዮጵያ በ500 ሚሊዮን ዩሮ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊሰማራ ነው

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ የ170 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ

የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ለታዳጊ ሀገሮች ተምሳሌት ነው፦ ቻይና

ባለስልጣኑ የተፈለገውን ያህል ግብር እየሰበሰበ አይደለም ተባለ

ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ 29 ሰልጣኞች በግጭት አፈታት ዙሪያ በኢትዮጵያ ስልጠና ወሰዱ

ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው እድገት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው- አይኤምኤፍ

በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ሁሉም አካላት በትብብ እንዲሰሩ ተጠየቀ

መማር ማስተማር ተስተጓጉሎባቸው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉበት ሁኔታ