Back

የጅቡቲ መንግሥት ልዑካን ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ላይ ለመሳተፍ ሰመራ ገቡ

ህዳር 27፣2010

በጅቡቲ መንግሥት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ነጂብ አብደላ ከማል የተመራ የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን በብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ላይ ለመሳተፍ ሰመራ ገባ፡፡

ልዑኩ ወደ ከተማዋ ሲገባ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና በከተማዋ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ 15ዐ የጅቡቲ የባህል ቡድን አባላትም ከልዑካኑ ጋር ገብተዋል፡፡

በተያያዘ በአፋር ክልል የሚገኙ የግል ኮሌጆች 12ኛውን የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ በጋራ ያዘጋጁት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም ሕብረ ብሔራዊነት፣ፌዴራሊዝምና ዴሞክራሲያዊ ብሔረተኝነት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ሕገ መንግሥቱ ሕብረ ብሔራዊነትን በማስተዋወቅ ሰዎች በማንነታቸው እንዲኮሩ ትልቅ እድል እንደፈጠረ በቀረበው ፅሁፍ ላይ ተገልጧል፡፡

በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማትና የሰላም ግንባታዎችን ሁሉም ዜጋ እንዲጠብቃቸው ለማስቻል የዴሞክራሲያዊ ብሔረተኝነት አስተሳሰብ እንዲያድግ መሰራት አለበት ተብሏል፡፡

ሪፖርተራችን አስማማው አየነው እንደዘገበው፡፡


የአፍሪካ ሃገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ ለቴክኖሎጂ ልማት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል - ክርስቲን ላጋርድ

ተርኪሽ ኢንደስትሪ ሆልዲንግ በኢትዮጵያ በ500 ሚሊዮን ዩሮ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊሰማራ ነው

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማትን ለማሳደግ የ170 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ

የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ለታዳጊ ሀገሮች ተምሳሌት ነው፦ ቻይና

ባለስልጣኑ የተፈለገውን ያህል ግብር እየሰበሰበ አይደለም ተባለ

ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ 29 ሰልጣኞች በግጭት አፈታት ዙሪያ በኢትዮጵያ ስልጠና ወሰዱ

ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው እድገት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው- አይኤምኤፍ

በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ሁሉም አካላት በትብብ እንዲሰሩ ተጠየቀ

መማር ማስተማር ተስተጓጉሎባቸው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉበት ሁኔታ