Back

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ችግር መረጋጋቱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ገለጸ

መስከረም 3፣2010

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ችግር መረጋጋቱን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ገለፁ፡፡

በትናንትናው ዕለት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከጅግጅጋና አወዳይ ከተሞች 6ዐዐ ያህል ነዋሪዎች ወደ ሐረር ከተማ ሸሽተው ገብተው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት የአገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ከሁለቱም ክልሎች አመራሮች ጋር በመሆን ግጭቱን መቆጣጠር መቻላቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የሁለቱን ክልሎች ተወላጆች ወደየመጡበት ከተማ የመመለስ ሥራም ተጀምሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር የመፍታት አቅም ያላቸው የሁለቱ ክልሎች ሕዝብና አመራሮች በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ሚንስትሩ አሳስበዋል፡፡

መረጃውን ያገኘነው ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ድረ ገፅ ነው፡፡


ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ ለምርጥ ዘር ልማት 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኙ

የብአዴን 37ኛው የምስረታ በዓል በባህርዳር ለታጋዮች እውቅና በመስጠት ተከብሯል

በአዲስ አበባ የሚጣሉ የፕላስቲክ ውጤቶች የከተማዋን ውበት እያበላሹ ነው

ወጣቶችን በማደራጀትና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ተጠየቀ

በባህርዳር ቢአኤካ በተባለ የግል ድርጅት የተቋቋመው የእምነበረድና ቀለም ፋብሪካ ተመረቀ

ብአዴን ለነባር ታጋዮች በሚሊንየም አዳራሽ የእውቅና ሽልማት ሰጠ

ብአዴን ህዝባዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአማራና ትግራይ ክልል ህዝቦች የጋራ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ ጉብኝት አደረጉ

ብአዴን ለህዝባዊ ወገንተኝነት በፅናት ሊታገል እንደሚገባ ተጠቆመ