Back

ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

ነሃሴ 6፤2009

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለመላው የኬንያ ሕዝብና በድጋሚ በፕሬዝዳንትነት ለተመረጡት ኡሁሩ ኬንያታ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በኬንያ በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ 54 በመቶ ድምፅ በማግኘት መመረጣቸውን የሀገሪቱ የምርጫና የድንበር ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡

የምርጫው ሂደት የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ስኬታማ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ለዚህ ውጤት መገኘት ታዲያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው መላው የኬንያ ሕዝብ የደስታ መግለጫ ያስተላለፉት ጠቅላይ ማኒስትር ኃይለማርያም በድጋሚ ለተመረጡት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታም እንኳን ደስ አሎት ብለዋል፡፡

ለመላው ኬንያውያንና በጠንካራ መሠረት ላይ ለተገነባው የኢትዮ-ኬንያ ግንኙነትም መጪው ጊዜ ብሩህ እንዲሆን አቶ ኃይለማርያም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡


የህዳሴ ግድብ በስርአተ ትምህርት ውስጥ አካቶ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ምሳሌ እንደሚያደርጋት ተገለፀ

በበጋው ወቅት ለሚከናወነው የመስኖ ስራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸው ተገለጸ

ብአዴን ከአማራ ክልል ውጪ ከሚሰሩ አመራሮቹ ጋር የሚያካሄደውን ጉባኤ ጀመረ

ኢትዮጵያ በፍትሃዊ የሥነ ፆታና ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አጥጋቢ ውጤት እያስመዘገበች ነው

ጃፓን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስድተኞች የ2.4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠች

ዴኢህዴን በክልሉ መቻቻልና አንድነት እንዲሰርጽ ማድረጉን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለፁ

የመገናኛ ብዙሀንን ሚና ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

እህትና አጋር ድርጅቶች ለደኢህዴን የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል