Back

የቻይናው ግዙፉ የኢንተርኔት ገበያ የአሊባባ መስራች ምስራቅ አፍሪካን ሊጎበኝ ነው

ሐምሌ 10፣ 2009

በአለማችን በኢንተርኔት የንግድ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ የሆነውና  አሊባባ የተባለው ኩባንያ መስራች ጃክ ማ  ምስራቅ አፍሪካን ሊጎበኝ ነው፡፡

ቱጃር ጃክ ማ  በኢስያ ስመጥር ከበርቴና የኩባንያው መስራችና ሊቀመንበር ነው፡፡

የቻይና ዜግነት ያለው ይህ ባለፀጋና የቢዝነስ ሰው በስራ ፈጠራ ዙሪያ ተሞክሮውን ለኬንያና ለሩዋንዳ ወጣቶች ለማካፈል በቀጠናው በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመጣ ተነግሯል፡፡

የ52 ዓመቱ ጃክ ማ በ30 ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ገንዘብ በኢስያ ቁጥር አንድ ከበርቴ እንደሆነም ይነገራል፡፡

ጃክ ማ ጉብኝቱን የሚያካሄደውም በናይሮቢ ኬንያ በሚካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት የንግድና የልማት ጉባኤ/ዮኤንሲቲኤዲ/ ላይ በወጣቶች ስራ ፈጠራና አንስተኛ ቢዝነስ ላይ ልዮ አማካሪ በመሆን ነው ተብሏል፡፡ 

በጉባኤውም ላይ ጃክ ማ ከዮኤንሲቲኤዲ ዋና ጽሐፊ ሙክሂሳ ኪቱዪ ጋር በመሆን ለ500 ወጣት የቢዝነስ መሪዎች ገለፃ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አንስተኛ የቢዝነስ አካላት እንዲሳተፉ ለማድረግ የመንግስታቱ ድርጅት ከጃክ ማ ጋር እንደሚሰራ ዋና ጽሐፊው ተናግረዋል፡፡

የአሊባባ ኩባንያ መስራች ጃክ ማ የአሁኑ የስኬት ህይወቱ ጋር ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ እንደሆነም ይናገራል፡፡

ባለው ሙያ ስራ ለማግኘት ሲያመለክትም ለበርካታ ጊዜዎች እንዳልተሳካለት እማኝነቱን ገልጿል፡፡

ባካበተው ሀብት የአለምችን 14ተኛ ቱጃር የሆነው ጃክ ማ፣ ታዳጊ ሀገሮች ኢኮኖሚያቸውን ለማበልፀግ ግብርና ህጎችን ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ የኮምፒውተር መረብ የንግድ ስርዓት እንዲጠቀሙ ይመክራል፡፡

ይህም አዳጊ አነስተኛ የቢዝነስ ተቋማትን እንዲያብቡ ያግዛል ሲል ተደምጧል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ ሲጂቲኤን 


የጸጥታው ምክር ቤት በአይ ኤስ አይ ኤስ የአሸባሪው ቡድን ላይ ውሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ የተረጋጋች ሶማሊያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ አሰታወቀች

በኮሪያ ባህረ ሰላጤ ያለው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጠየቁ

የመስቀል በአልን የቱሪስት መስህብ ለማድረግ እየተሰራ ነው:- የባህልና የቱሪዝም ሚኒስቴር

የአፍሪካን ግብርናን ለማሳደግ ኢትዮጵያ ልምዷን ታካፍላለች፦ጠ/ሚ ኃይለማርያም

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ትምህርት ቤት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር ያላትን ትብብር ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች

የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ጥረት አደነቁ

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ