Back

ኢትዮጵያ የቻይና፣ ኮሪያና ህንድ የአልባሳት አምራቾችን እየሳበች መሆኑ ተገለፀ

ሐምሌ 10፣2009

ኢትዮጵያ የቻይና ኮሪያና ህንድ  የአልባሳት አምራቾችን እየሳበች መሆኑ ተገለፀ፡፡

ኤስያ ሪቪው የተባለው ደረ ገፅ እንደዘገበው ወጣት የሰራተኛ ኃይል መኖሩና ለኢንቨስትመንት አመቺ ሁኔታዎች እተፈጠሩ መምጣታቸው  የኢስያ አለባሳት አምራች ኩባንያዎችን ለመሳብ አስችላል፡፡

በተለይም የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር መገንባት ለወጪ ምርት ገበያው አመችነት ሲባል በጨርቃጨርቅና አልባሳት ላይ የተሰማሩት ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እያስቻለ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

ለአብነት በቦሌ ለሚ የኢንዱስተሪ ፓርክ የተሰማሩትን  የቻይና፣የታይዋንና የደቡብ ኮሪያ  በጨርቃጨርቅ፣በአልባሳትና በቆዳ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በአንድ ማዕከል አምርተው ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የያዙት ጥረት ትልቅ  ተሰፋ ሰጪ ጅምር መሆኑም ዘገባው ያስረዳል፡፡

ዘጋቢው የደቡብ ኮሪያ  የሺን የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ስራ አስኪያጁን ጠይቆ ኩባንያው የሚያመርታቸውን የስፖርት አልባሳት 60 በመቶውን ለአውሮፓ፣20 በመቶውን ለአሜሪካና ቀሪውን ለኢስያ ገበያ እንደሚያቀርብ ጠይቆ በዘገባው አመልክቷል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት ኩባንያዎች የኢስያ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ፒቪኤች ያሉ አለም አቀፍ መለያ ያላቸው ልብሶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን ኢስያ ኒኬይ ዘግቧል፡፡


የጸጥታው ምክር ቤት በአይ ኤስ አይ ኤስ የአሸባሪው ቡድን ላይ ውሳኔ አሳለፈ

ኢትዮጵያ የተረጋጋች ሶማሊያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ አሰታወቀች

በኮሪያ ባህረ ሰላጤ ያለው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጠየቁ

የመስቀል በአልን የቱሪስት መስህብ ለማድረግ እየተሰራ ነው:- የባህልና የቱሪዝም ሚኒስቴር

የአፍሪካን ግብርናን ለማሳደግ ኢትዮጵያ ልምዷን ታካፍላለች፦ጠ/ሚ ኃይለማርያም

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ትምህርት ቤት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

ኢትዮጵያ ከኩባ ጋር ያላትን ትብብር ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች

የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ጥረት አደነቁ

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ