Back

ጨፌ ኦሮሚያና የአማራ ክልል ምክር ቤት ያለፈው በጀት አመት አፈፃፀማቸውን እየፈተሹ ነው

ሐምሌ 08፣2009

ጨፌ ኦሮሚያና የአማራ ክልል ምክር ቤት  በመደበኛ ጉባኤያቸው  ያለፈውን በጀት  አመት አፈፃፀማቸውን እየፈተሹ ነው፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ ማካሄድ በጀመረው 2ተኛው ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤው የክልሉን የ2ዐዐ9 በጀት አመት የስራ እቅድ አፈፃፀም አዳምጧል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በሪፖርታቸው ትኩረት ሰጥተው ካቀረቧቸው ጉዳች መካከል  በክልሉ የግብርና ምርታማነትና የስራ ዕድል ፈጠራ ይገኝበታል፡፡

በ2009 የምርት ዘመን በክልሉ 143.9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቷል ያሉት  ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በበጀት ዓመቱ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደስራ ማስገባት መቻሉ ከተመዘገቡ ተጨባጭ ለውጦች መካከል እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡ለወጣቶቹም የ2.5 ቢሊዮን ብር ብድርና የመስሪያ ቦታ ማግኘታቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

በኢንቨስትመንት ስም በክልሉ ያለ አግባብ ተይዞ የቆየ  ከ50ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ገቢ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በሌሎች ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ዘርፎች የተከናዋኑ ስራዎችም ለጨፌው ቀርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት  በ2ዐ1ዐ በጀት ዓመትም በህብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል እቅድ ነድፎ ክልሉ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ከጥልቅ ተሃድሶው በኋላ የተገኙ ለውጦች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ ለማ አመልክተዋል፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ በቀጣይ ቀናትም የ2010 በጀትን የማፅደቅ ስራና የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተርን 2009 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምን እንደሚያዳምጥ  ሪፖርተራችን ሙባረክ ሙሐመድ ከአዳማ ዘግቧል።    

በተያያዘም ዜና የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤትም  ትላንት በጀመረው  በ2ተኛው ዓመት የስራ ዘመን 7ተኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገንዱ አንዳርጋቸው የቀረበውን የ2009 የስራ አፈፃፀም ረፖርት አዳምጧል፡፡

አቶ ገዱ እንዳሉት ባለፈው በጀት ምንም እንኳንክልሉን  የፀጥታ አለመረጋጋት ገጥሞት የነበረ  ቢሆንም እቅዱን ለማስፈፀም ጥረት ተደርጓል፡፡ይሁን እንጂ እቅዱን በማፅፈፀም ሂደት በአመራሩና በፈፃሚ አካሉ  የተሟላ የክትትልና ድጋፍ እጥረት መስተዋሉን በሪፖርታቸው አስረድተዋል፡፡

በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለመከላከልም ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ርብርብ በዩኒቨርስቲዎች በሙከራ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን አስተባብሮ ማገዝ እንደሚገባ  በጉባኤው ላይ ተመልክቷል፡፡

በስራ ላይ ያለው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም መንግስትና ህዝብ ተግባብተው እንዲሰሩ ማስቻሉን በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው የባለፈው በጀት ዓመትን በማህበራዊ፣በኢኮኖሚያዊና በሌሎች ዘረፎች የተሰሩ ስራዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት በሚቀጥሉት ሶስት ቀናትም እንደሚቀጥል ሪፖርተራችን ኮሰን ብርሃኑ ከባህርዳር ባደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡

 


የኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ግንኙነት ሊጠናከር ይገባል- ፕ/ት ሙላቱ ተሾመ

በምዕራብ ጉጂ ድርቁ የምርት እጥረት ሊያስከትል ይችላል

በባህርዳር የመብራት መቆራረጥ ችግር እየተባባሰ ነው

የአካባቢ ሃብት ብክለትና ብክነትን ለመከላከል ትኩረት ሊሰጥ ይገባል

ለሀገሪቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የውጪ ዜጎች የዜግነት መታወቂያ ሊሰጥ ነው

የከተማ አስተዳደሩ በቆሻሻዎች የተዘጉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮችና ቱቦዎች ጠረጋ እያካሄደ ነው

ከዕፀዋት የተቀመመ ተምችን የሚያጠፋ መድሃኒት በሙከራ ማግኘቱን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ

ሳውዲ የምህረት አዋጁን በድጋሚ ለአንድ ወር አራዘመች

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለ12 አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ