Back

የሚንስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ሐምሌ 7፣2009

የሚንስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ጋር ተናቦና ተመጋግቦ ለመሄድ የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራርን በተመለከተ በቀረበ  ረቂቅ  ደንቡ ላይ ከተወያየ በኃላ ማሻሻያዎች ታክለውበት ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና ስራ ላይ እንዲውል  ወስኗል፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እና አከባቢያዊ የንግድ ግንኙነትና ድርድር ጉዳዮች መመሪያ  በተመለከተም   በምክር ቤቱ  ውይይት ከተካሄደበት በኃላ ማሻሻያዎች ታክለውበት መመሪያው ስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል፡፡

ኒውኤራ ማይኒንግ ፒ.ኤልሲ የተባለ ኢትዮጵያዊ ኩባንያ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ጉሪጌ ዞን ፣ ሶዶ ወረዳ ልዩ ስሙ ኬላ በሚባል ቦታ ላይ የከፍተኛ ደረጃ የሲልካ ሳንድ ማዕድን የማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ኩባንያው በህጉ መሰረት የሚፈለጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟላ መሆኑ ስለተረጋገጠ ኩባንያው የጠየቀው የከፍተኛ ደረጃ የሲልካ ሳንድ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ስምምነት በምክር ቤቱ ተቀባይነት ስላገኘ ስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር በኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ፣ በስታንዳርድ የባቡር ኔትዎርክ ዝርጋታ አሰራርና አስተዳደር፣ በሞያሌ ድንበር ጣቢያ የጋራ ቁጥጥር፣ ሥነ-ሥርዓት፣ አገልግሎቶች እና አስተዳደር፣ በአየር ትራንስፖርት፣ በመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በቱሪዝም ዘርፍ እና የጠቅላላ ትብብር 1ዐ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡

ስምምነቶቹ ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙና የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትስስሩን ለማጠናከር ስለሚረዱ እንዲፀድቁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡


ብአዴን ለህዝባዊ ወገንተኝነት በፅናት ሊታገል እንደሚገባ ተጠቆመ

በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ውጤታማ የሆኑ 641 አርሶና አርብቶ አደሮች፣ እንዲሁም ተመራማሪዎች ተሸለሙ

የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ መረጋጋት እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑን ለአሜሪካ ኮንግረስ አበላት ገለፀ

በ37 ዓመታት የብአዴን ጉዞ በትግሉ መስዋዕት የሆኑ ታጋይ ሰማዕታትም እየተዘከሩ ነው

ገዳ የትራንስፖርት ኩባንያ ወደ ሃገር ያስገባቸውን የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አስመረቀ

ፖሊስ ኮሚሽኑ 173 ሞተረኛ የትራፊክ ፖሊሶችን አስመረቀ

አርሶ አደሮች ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሚያገኙት ትምህርት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ

የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተጀመረ

የግብርና እና የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፎችን በዘመናዊ አሰራር ማከናወን ይገባል- ብአዴን