Back

የፓስፖርት እደላ በፖስታ አገልግሎት ድርጅት ሊሰጥ ነው

ግንቦት 11፣2009

የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ  ዋና መምሪያ  እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት  የፓስፖርት እደላ በፖስታ አገልግሎት ለመስጠት  ተስማሙ፡፡

የስምምነቱ አላማም ደንበኞች ጥራት ያለውና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የፓስፖርት እደላው የተቀላጠፋ ለማድረግ አስፈላጊ ቁሳቁሶችና የሰው ሃይል በማሟላት ስራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት ስራውም ግንቦት 3/2009 ዓ.ም ጠቅላይ ፖስታ ቤት በይፋ  ተጀምሯል፡፡

በአሁን ሰአት የፓስፖርት እደላው  እየተካሄደ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ በዋናው ፖስታ ቤት ሲሆን በቀጣይ  በአዲስ አበባ ለደምበኞች አመቺ በሆኑና በተመረጡ የድርጅቱ አገልግሎት መስጫ ጣብያዎች  እንደሚከናወን  ተገልጿል፡፡

በቀጣይም አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በክልሎች፣ በዞኖችና በወረዳዎች ለማስፋፋት  ጥናት እየተደረገ እንደሆነ  የአትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

በድርቤ መገርሳ


በጅማ በሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተይዞ የቆየ መሬት ለ380 ለአከባቢው ወጣቶች ተሰጠ

ኢትዮጵያ አቶ ነዋየ ክርስቶስ ገብረአብን ለአፍሪካ ሕብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነርነት በእጩነት አቀረበች

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

ኢትዮጵያና ሩሲያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የአማራ ክልል አርሶ አደሮች የማዳበሪያ ዋጋ ከአቅርቦቱ ጋር እንዳልተመጣጠነላቸው ገለጹ

29ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል

የወንዶገነት የደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ያሰለጠናቸው 338 ተማሪዎችን አስመርቋል

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በአስተዳደር ስርዓት ግንባታ ላይ ተባብረው ለመስራት ተስማሙ

የእስልምና እምነት ተከታዮች በሀገሪቱ እድገት ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ነው- ከንቲባ ድሪባ ኩማ