Back

በኢትዮጵያ ሶማሌ ተከሰቶ የነበረው የአተተ በሽታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

ግንቦት 11፣2009

የኢትዮጵያ  ሶማሌ ክልል ተከሰቶ የነበረውን የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ᎓᎓

በኢትዮጵያ  ሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በተከሰተው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በክልሉ ባሉ 9 ዞኖች ውስጥ በ10ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በወረርሽኙ መጠቃታቸው ይታወሳል᎓᎓ በቆራሂ ዞን  ቀብሪ ዳሃር ወረዳ በሽታው በስፋት ከተከሰተባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው᎓᎓

ይህንን ወረርሽኝ ለመግታት በፌዴራልና በክልሉ  አስተዳደር በተደረገው ዘመቻ ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል᎓᎓

አቶ ዚያድ ኑር አብዲ  የቀብሪ ዳሃር ሆስፒታል ሃላፊ " አጠቃላይ ዞኑ አንድ ኬዝ ብቻ ነው ሪፖርት የተደረገው ፣ይህ ማለት ግራፉ እንዳለ  ባጭሩ ተቀየረ ማለት ይቻላል" ሲሉ ገልፀዋል᎓᎓

እንደ ቀብሪዳ ሃር ወረዳ ሁሉ በክልሉ ውስጥ ወረርሽኙ ተከስቶባቸው  የነበሩ ሌሎች ወረዳዎችም ላይ በሽታውን መቆጣጠር መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃሰን እስማኤል ተናግረዋል᎓᎓

"ከጤና ጥበቃ  ከተለያዩ አጋር  ድርጅቶች ጋር ክልሉ ባደረገው ርብርብ ተከስቶ የነበረውን የአተት በሽታ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ተችሏል᎓᎓"

ወረርሽኙ ዳግም በክልሉ እንዳይከሰትም የቅድመ መከላከል ትምህርት   ለህብረተሰቡ እየተሰጠ መሆኑን እና የቅድመ መከላከል ስራ የሚሰራ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል᎓᎓

ሪፖርተር  ፡‑ ሜሮን በረዳ

 


የትራንስ አፍሪካ ሀይዌይ አካል የሆነው ከሀዋሣ ሞያሌ የመንገድ ግንባታ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፍሎ እየተከናወነ ነው

ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ከግብፅ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቦሊ ጋር በግብፅ መከሩ

የወላጆቻቸውን የዓላማ ፅናትና ህዝባዊነት ጠብቀው ለትውልድ እንደሚያስተላልፉ የትግራይ ሰማዕታት ልጆች ተናገሩ

የእንቦጭ አረም በቆቃ ሀይቅ ላይ በከፍተኛ ደረጃ መዛመቱ ተጠቆመ

ወደ ቻይና በትምህርት ዕድል ስም በህገ ወጥ ደላሎች የሚላኩ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ለዕንግልት ተዳርገዋል ተባለ

በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መብት ለማስከበር በትኩረት እንደሚሰራ በአገሪቱ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አስታወቀ

ወጣቶችን ለህገ ወጥ ስደት በሚዳርጉ ችግሮች ላይ በስፋት እንዲሰራ የሽሬ እንዳስላሴ ነዋሪዎች ጠየቁ

በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ሃይል ባለመለቀቁ ተጠቃሚ አልሆንም:- የምእራብ ጉጂ ዞን አርብቶ አደሮች

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ጋር ተወያዩ