Back

የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ዕድሎች ያስተዋወቀ ፎረም በቻይና ተካሄደ

ግንቦት 11፣2009

የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ዕድሎች ያስተዋወቀ ፎረም በቻይናዋ ፉጅያን ግዛት ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መዋቅራዊ ሽግግር ለማድረግ በጀመረችው ጥረት ላይ ሰፊ የሰው ሀይል ለሚጠቀምና ጥራት ላለው የቻይና ኢንቨስትመንት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ደቡብ ምስራቋዊቷ ፉጂያን የኢትዮ ቻይና ፉጂያንን  የኢንቨስትመንት ፎረምን  አስተናግዳለች፡፡

በፎረሙ የኢትዮጵያን ልዑክ በመምራት ወደ ፉጂያን ያመሩት ጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማርያም ደሳለኝ  ኢትዮጵያ ጥራት ላላቸው የቻይና  የኢንቨስትመንቶች ትኩረት በመስጠት ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት ዕውን  ለማድረግ ትሰራለች ብለዋል፡፡

ሪፖርተራችን አብዲ ከማል ከቦታው እንደዘገበው  በፎረሙ ከተሳተፉት ኩባንያዎች የተወሰኑት በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና መሰረተ ልማት ግንባታ መሳተፍ የጀመሩና ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ  ያሉ ናቸው ፡፡

ከነዚህ መካከል በጨርቃጨርቅና አልባሳት በአለም ደረጃ የሚታወቀው  የፍላይን ቡድን የዊና የጉዋንግ  ፉሺንግ ኩባንያዎች የተናጠል ውይይቶችንም ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር አድርገዋል፡፡

የፉጂያን ግዛት አስተዳዳሪና ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር   ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተራችን አብዲ ከማል ከቻይና ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል።


የህዳሴ ግድብ በስርአተ ትምህርት ውስጥ አተካቶ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ምሳሌ እንደሚያደርጋት ተገለፀ

በበጋው ወቅት ለሚከናወነው የመስኖ ስራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸው ተገለጸ

ብአዴን ከአማራ ክልል ውጪ ከሚሰሩ አመራሮቹ ጋር የሚያካሄደውን ጉባኤ ጀመረ

ኢትዮጵያ በፍትሃዊ የሥነ ፆታና ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አጥገቀቢ ውጤት እያስመዘገበች ነው

ጃፓን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስድተኞች የ2.4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠች

ዴኢህዴን በክልሉ መቻቻልና አንድነት እንዲሰርጽ ማድረጉን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለፁ

የመገናኛ ብዙሀንን ሚና ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

እህትና አጋር ድርጅቶች ለደኢህዴን የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል