Back

በተመድ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ዶ/ር ቴድሮስን እንደሚደግፉ ገለጹ

ግንቦት 10፣ 2009

ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት እየተወዳደሩ የሚገኙትን ኢትዮዽያዊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የማይዋዥቅ ድጋፍ እንዳላቸው ገለጹ ተመድ የአፍሪካ ተወካይ ቴቴ አንቶንዩ ገለጹ፡፡

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቡድን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ከአምስት ቀን በኋላ አመታዊ የአለም የጤና ቀን ስብሰባ በሚካሄድበት በግንቦት 15 እንደሚከናወን ይጠበቃል᎓᎓

የአፍሪካ የአምባሳደሮች ቡድን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ቢመረጡ በአለም የጤና ጅርጅት የሚፈለገውን አዲስ ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል᎓᎓

ዶክተሩ ሳይንሳዊና ዲፕሎማሲያዊ ክህሎት እንዳላቸውና የእርሳቸውን የምረጡኝ ዘመቻ  ከጎን ሁነው እንደሚደግፉ አረጋግጠውላቸዋል᎓᎓

ከኢትዮዽያ ከሞዛምቢክ ከቻድ ከሩዋንዳ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐፕሊክ ከማሊ የተውጣጡ አምባሳደሮቹ አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ከአፍሪካ አንድም ሰው ተመርጦ እንደማያውቅና ይህ ሁኔታ ግን በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መቀየር እንዳለበት ገልፀዋል᎓᎓

ምንጭ፤ እንተለክቹዋል ፕሮፐርቲ ዎች


የህዳሴ ግድብ በስርአተ ትምህርት ውስጥ አካቶ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገው ጥረት ምሳሌ እንደሚያደርጋት ተገለፀ

በበጋው ወቅት ለሚከናወነው የመስኖ ስራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸው ተገለጸ

ብአዴን ከአማራ ክልል ውጪ ከሚሰሩ አመራሮቹ ጋር የሚያካሄደውን ጉባኤ ጀመረ

ኢትዮጵያ በፍትሃዊ የሥነ ፆታና ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አጥገቀቢ ውጤት እያስመዘገበች ነው

ጃፓን በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ ስድተኞች የ2.4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጠች

ዴኢህዴን በክልሉ መቻቻልና አንድነት እንዲሰርጽ ማድረጉን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለፁ

የመገናኛ ብዙሀንን ሚና ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ

እህትና አጋር ድርጅቶች ለደኢህዴን የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል