Back

ኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነታቸውን በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ገለፁ

መጋቢት  11፣2009

ኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነታቸውን በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንሚገባ  ገለፁ፡፡

የቻይናው ፕሬዝዳንት የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ያንግ ጄይቺ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግስት ውይይት አድርገዋል፡፡

በሌላ በኩል የቻይና ወዳጅነት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ልዩ ስፍራ እንደሚሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

ያንግ ጄይቺ በበኩላቸው  የሁለቱ ሃገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ጭምር ተምሣሌት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም በያንግ ጄይቺ የሚመራውን የቻይና ልዑክ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ያንግ ዬቺ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር ለቻይና-አፍሪካ ግንኙነት መጠናከር በአርአያነት የሚወሰድ ነው።

ያንግ ዬቺ እንዳሉት ቻይና እያደገ ለመጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ድጋፍና ትብብር ታጠናክራለች።

የቻይናው ፕሬዝዳንት የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ያንግ ጄይቺ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በተለያዩ የሁለቱ አገራት ትብብርና ወዳጅነት ዙሪያ ምክክር ማካሄዳቸው ለቀጣይ ትብብር ወሳኝ ነው ሲሉ መናገራቸውን የአቢሲ ሪፖርተሮች ዘግበዋል፡፡


የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለፍሬ እንዲበቃ ህዝቡ ከጎኑ ተሰልፎ የድርሻውን እንዲወጣ ኦህዴድ ጥሪ አቀረበ

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ39 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ቦንድ ገዝተዋል

የሶማሊያ ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም የኢጋድ ሀገራት ተስማሙ

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የአስፈጻሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ዋነኛ ማነቆ ነው-ጥናት

ኦህዴድ የህዝቡን ጥያቄና ቅሬታ ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ

የኦሞ ኩራዝ የመስኖ ልማት ኘሮጀክት የምእራፍ 1 እና 2 የግንባታ ስራዎችን ለማከናወን ስምምነት ተፈረመ

የህዳሴ ግድብ የተጀመረበት 6ኛ ዓመትን አስመልክቶ አገር አቀፍ የፓናል ውይይት በመቐለ ተካሄደ

ባለሥልጣኑ 23 ቶን የተበላሹ ምግቦች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረጉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶስት አገራት አዲስ በረራ ሊጀምር ነው