Back

የአፍሪካ ህብረት ለሶማሊያ ዘላቂ ሰላም ድጋፉን እንደሚያጠናክር ገለፀ

መጋቢት  11፣2009

አፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዲሱ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂ ማሀማት አስታወቁ፡፡

 

ሊቀመንበሩ ይህን የተናገሩት የህብረቱን መንበረ ስልጣን ከተረከቡ ከአራት ቀናት በኃላ ሶማሊያን በይፋ በጎበኙበት ወቅት ነው ፡፡

የህብረቱ ኮሚሽነር በጉብኝታቸው ከአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ጋር አገሪቱ እየገጠማት ባለው ቀውስ ዙሪያ በሞቃዲሾ መክረዋል፡፡ 

በዚህም በሶማሊያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት አፍሪካ ህብረት የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል፡፡     

በሶማሊያ የተሳካ አጠቃላይ ምርጫ እንዲከወን የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠር ሂደት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል/አሚሶም/ ከአገሪቱ የፀጥታ ሀይል ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷልም ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዝናብ እጥረት ሳቢያ ሶማሊያ የተጋረጠባትን የድርቅ አደጋ ለመቋቋም በምታደርገው ጥረት ህብረቱ የድርሻውን ይወጣል ብልዋል፡፡ 

በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ህይወታቸውን መስዕዋት ላደረጉ ለአሚሶም፣ ለሶማሊያ ፀጥታ ሀይሎችና ሰላማዊ ዜጎች የህብረቱ ሊቀመንበር ክብር ይግባቸዋል ብለዋል፡፡

በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ በበኩላቸው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር በመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው  ሶማሊያን መምረጣቸው ለሀገሪቱ የሰላም ጥረት ምን ያህል ትኩረት እንደሰጡ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ሪሊፍ ዌብ


የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሁሉንም የባለድርሻ አካላት ድግፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

የባለ 5 እና 10 ብር ሞባይል ካርዶች ለክልሎች እየተሰራጩ ነው

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚዘረዝር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ወንጀለኞችን ለመለዋወጥ የተደረሰበትን ስምምነት አፀደቀች

ኤምባሲው በኬኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈታ

መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአህጉሪቱ የፀጥታ ጉዳዮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል፡- ሙሳ ፈቂህ መህመት

የመሰረተ ልማት ሂደቱን ለማቀላጠፍ ተቋማቱ በጋራ እየሰሩ ነው

ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ላይ ተስማሙ