Back

ካናዳዊቷ መምህር የዓመቱ ምርጥ ተብላ የ1 ሚሊዮን ዶላር አሸነፊ ሆናለች

መጋቢት 11፣ 2009

በየ ዓመቱ በሚካሄደው የዓመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት ካናዳዊቷ ማጂ ማክዶኔል የዓመቱ ምርጥ መምህር ተብላ የ1 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ለመሆን በቅታለች፡፡

በውድድሩ ከተለያዩ አህጉራት የተወጣጡ 20ሺህ መምህራን ተሳትፍዋል፡፡

ህልሜ አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ትውልድ መፍጠር ነው ስትል ተሸላሚዋ ማጂ ተናግራለች፡፡

ተሸላሚዋ ማጂ በካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሪዶ የመጪውን ዘመን ቀራጭ ተብላ ተሞካሽታለች፡፡

በአርክቲክ በረዶ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናትን ፈጠራ በታከለበት መንገድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድርጓ  የተሸላሚዋ ልዩ ጥረት ተብሏል፡፡

ሽልማቱን ያበረከተው አከባቢና ትምህርት ጥራት የሚሰራው ቫርኪ ፋውንዴሽን የተባለ ድርጅት ነው፡፡

ምንጭ፡-ዩሮ ኒውስ

የትራንስ አፍሪካ ሀይዌይ አካል የሆነው ከሀዋሣ ሞያሌ የመንገድ ግንባታ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፍሎ እየተከናወነ ነው

ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ከግብፅ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቦሊ ጋር በግብፅ መከሩ

የወላጆቻቸውን የዓላማ ፅናትና ህዝባዊነት ጠብቀው ለትውልድ እንደሚያስተላልፉ የትግራይ ሰማዕታት ልጆች ተናገሩ

የእንቦጭ አረም በቆቃ ሀይቅ ላይ በከፍተኛ ደረጃ መዛመቱ ተጠቆመ

ወደ ቻይና በትምህርት ዕድል ስም በህገ ወጥ ደላሎች የሚላኩ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ለዕንግልት ተዳርገዋል ተባለ

በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መብት ለማስከበር በትኩረት እንደሚሰራ በአገሪቱ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አስታወቀ

ወጣቶችን ለህገ ወጥ ስደት በሚዳርጉ ችግሮች ላይ በስፋት እንዲሰራ የሽሬ እንዳስላሴ ነዋሪዎች ጠየቁ

በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ሃይል ባለመለቀቁ ተጠቃሚ አልሆንም:- የምእራብ ጉጂ ዞን አርብቶ አደሮች

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ጋር ተወያዩ