Back

ቻይና ምጣኔ ሀብቷ ፈጠራን መሰረት አድርጎ እንዲያድግ አዲስ አቅጣጫ መትለሟን ገለፀች

መጋቢት  11፣2009

ቻይና ምጣኔ ሀብቷ  ፈጠራን  መሰረት አድርጎ እንዲያድግ አዲስ አቅጣጫ መትለሟን ገለፀች፡፡  

የአገሪቱ  ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ዣንግ ጋኦሊ በቻይና የልማት ፎረም ላይ ተገኝተው እንዳሉት የፈጠራ ስራዎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ  እንዲመነደግ  የሚያደርግ  አቅም እንዲፈጠር የሚያስችል አሰራር ትከተላለች፡፡ ይህም  እድገቱን  ትክክለኛ የምጣኔ ሀብት ይዞታ እንዲኖረው ያስችላል ብለዋል፡፡

በተለይም ቻይና በሳይንስና ቴክኖሎጂ  መስክ ያላትን አቅም በማሻሻል ፈጣን እድገት የሚያሳዩ ዘርፎችን በአጭር ጊዜ  እንዲያብቡ ለማድረግና ተለምዷዊ አሰራር  የሚከተሉ ኢንዱስትሪዎች ወደ ዘመናዊነት እንዲቀየሩ ትጥራለች ብላዋል ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ዣንግ ጋኦሊ ፡፡  

በጉባኤው ላይ መንግስት  የስራ ፈጠራን እንደሚያበራታታና የገበያውን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል  የኢንተርኔት አሰራር ጥቅም ላይ እንደሚውልም ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የገንዘብ ነክና በታላላቅ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የለውጥ ማሻሻያ እንደምታደርግ ቻይና በመድረኩ ላይ አስታውቃለች፡፡

የቻይና የልማት ፎረም  በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ፖሊሲ አውጪዎች ጭምር የተሳተፉበት መድረክ መሆኑን ሽንዋ ዘግቧል፡፡  


የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሁሉንም የባለድርሻ አካላት ድግፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

የባለ 5 እና 10 ብር ሞባይል ካርዶች ለክልሎች እየተሰራጩ ነው

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚዘረዝር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ወንጀለኞችን ለመለዋወጥ የተደረሰበትን ስምምነት አፀደቀች

ኤምባሲው በኬኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈታ

መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአህጉሪቱ የፀጥታ ጉዳዮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል፡- ሙሳ ፈቂህ መህመት

የመሰረተ ልማት ሂደቱን ለማቀላጠፍ ተቋማቱ በጋራ እየሰሩ ነው

ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ላይ ተስማሙ