Back

የህብረቱ መሪዎችና የኢንዱስትሪው ዘዋሪዎች ውይይት ተጀመረ

መጋቢት 11፣ 2009

የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት ለማሸሻል መሪዎች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ቁልፍ ሚና ያላቸውን ባለሀብቶች እንዲሁም የዘርፉን ሙህራን ያካተተ ውይይት ዛሬ በሞሪሸስ ተጀምሯል፡፡

ከመጋቢት 11­-13 2009 ዓ.ም ድረስ የሚደረገው ውይይት የአፍሪካን ዕድገት ለማፋጠን የታቀደውን የምጣኔ ሀብት ግብ መሰረት ያደረገ ነው፡፡

አፍሪካን ኢኮኖሚክ ፕላትፎርም የተሰኘው ጉባዔ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት እንዴት መጠቀም እንዳለባት አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

ጉባኤው የአህጉሪቱን ምቹ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን ለይቶ መፍትሔ እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል፡፡

በሀገራቱ መካከል የምጣኔ ሀብት ትስስርን በማሳደግ ከዓለም ገበያ ባለድርሻነትን ማሳደግ የሚቻልበትን መንገድም ያመላክታል ትብሎ ይጠበቃል፡፡

ለንግድ ማነቆ የሆኑ ፖሊሲዎችን ማስወገድ ዋና ግቡ አድርጎ የሚሰራው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ፕላትፎርም በኢንዱስቱሪ፣ በአፍሪካ እርስ በእርስ ንግድ፣ በነጻ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ክህሎት በማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፣ የአፍሪካ ህብረት


የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሁሉንም የባለድርሻ አካላት ድግፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

የባለ 5 እና 10 ብር ሞባይል ካርዶች ለክልሎች እየተሰራጩ ነው

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚዘረዝር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ወንጀለኞችን ለመለዋወጥ የተደረሰበትን ስምምነት አፀደቀች

ኤምባሲው በኬኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈታ

መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአህጉሪቱ የፀጥታ ጉዳዮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል፡- ሙሳ ፈቂህ መህመት

የመሰረተ ልማት ሂደቱን ለማቀላጠፍ ተቋማቱ በጋራ እየሰሩ ነው

ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ላይ ተስማሙ