Back

ክልላዊ መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረጉ ነው

መጋቢት 9፣ 2009

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የቆሻሻ ክምር መደርምስ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች የተለያዩ ክልላዊ መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡

የደቡብ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 5 ሚሊዮን ብር፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ የሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 5ዐ4 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ 1 ሚሊዮን ብር፣ የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሰራተኞች 4ዐሺ 381 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት የከተማው አስተዳደር ከህዝብ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልፀው ተጎጂዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር፤ አባዲ ወይናይ


በኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የሚነሱ የሕዝብ ቅሬታዎችን ይፈታል የተባለ የሥራ መመሪያ ተዘጋጀ

የመቐለ ከተማ ወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ የሥራ ዕድል በማግኘታቸው ኑሮአቸው መሻሻሉን ገለፁ

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ት/ሚ ገለጸ

የአዳማና ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በያዝነው ወር መጨረሻ ይመረቃሉ

የኃይማኖት አባቶች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ

በአገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ኢህአዴግ የተመጣጣኝ ውክልና ድርሻ 15 በመቶ እንዲሆን ተደራደረ

በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ሲከሰት የነበረው ሁከት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ክልሉ አስታወቀ

መሬት ወስደው ባላለሙ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የጅማ ከተማ አስተዳደር ገለፀ

የህዳሴ ግድብ በስርአተ ትምህርት ውስጥ አካቶ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ