Back

ለአደጋ በሚያጋልጡ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ከአደጋ ቀድሞ ለመጠበቅ በትኩረት ይሰራል፡- ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ

መጋቢት 9፣ 2009

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው አደጋ ለከተማ አስተዳደሩ ብቻም ሳይሆን ለሀገር ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተናሩ፡፡

ሚንስትሩ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ቆሼ ላይ በደረሰው አደጋ አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል መፍጠን እንዳለብን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ የወንዝ ዳረቻዎች የሚኖሩ ዜጎች ችግር እንዳይደርስባቸው አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚሰራ ተናረዋል ዶ/ር ነገሪ፡፡

በዘላቂነት ግን ለከተማዋ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን የከተማዋን የመኖሪያ አካባቢ ምቹ ለማድረግ የሚያግዝ በመሆኑ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከቴክሳስ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር  ቆሼ ላይ አደጋው እንዴት እንደተፈጠረ የሚያጠና ቡድን ለማቋቋም እየተሰራ ነው ያሉት ሚንስትሩ የችግሩ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተጠናቀቀው ሳምንት ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂ ጎሳዎች በጋምቤላ በኩል ገብተው ህጻናትን አፍነው ወስደዋል ንብረትም ዘርፈዋል ያሉት ሚንስትሩ ህጻናቱን ለማስመለስ በተደረገው ጥረት ስድስት ህጻናት ሲመለሱ ተወስደው የነበሩ 185 ከብቶችንም ማስመለስ ተችሏል ብለዋል፡፡

እንዲህ ያለው ችግር ተደጋጋሚ እየሆነ በመሆኑ እና የደቡብ ሱዳን መንግስት የማይወክሉ ጉሳዎች በመሆናቸው በተለይ ወደ አገራችን የሚገቡበትን መስመር በመለየት ቅኝት ይደረጋል ብለዋል ሚንስትሩ፡፡

የአባይ የትብብር ማዕቀፍን የፈረሙ አገራት በፓርላማቸው እንዲያጸድቁ እና ለተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ክትትል በትኩረት እያከናወነች ነው ብለዋል ሚንስትሩ፡፡

በኤርትራ ጉዳይ ላይ መንግስት የፖሊሲ ለውጥ አለማድረጉን የገለጹት ዶ/ር ነገሪ የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት ለማሻሻል ግን አዲስ ፖሊሲ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ወሰን ላይ በሚገኙ ወረዳዎች የነበረው ግጭት መሰረቱ ከመሬት ጋር የተያያዘ ቢሆንም አሁን ግን ሁለቱ ክልሎችና ፌደራል መንግስት ባደረጉት ጥረት ጉዳዩን ማርገብ ተችሏልም ብለዋል፡፡

ግጭቱ ያስነሱና እንዲባባስ ያደረጉ አካላት ላይ ግን መንግስት ፈጣን እርምጃ እንደሚወስድ ዶ/ር ነገሪ ከጋዜጠኖች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ጌቱ ላቀው       


ከኢትዮጵያ ሴት የፓርላማ ኮከስ አባላት ጋር መስራት እንደሚፈልጉ የሱዳን ሴት የፓርላማ አባላት ተናገሩ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ዘርፍ ያሰለጠናቸው 245 ተማሪዎችን አስመረቀ

በዩኒቨርስቲዎች ላይ የተፈጠረው የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎል አሳስቦኛል:- የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር

የቀይ ሽብር ተከሳሹ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

በርካታ የግል ጤና ተቋማት በግለሰብ ህንፃ ላይ ተከራይተው አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው

የኢትዮጵያ የውሃ ሃብት አያያዝ ዘመናዊና በመረጃ የተደገፈ መሆን እንዳለበት ተጠቆመ

የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የተጀመረው ንቅናቄ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ በጥሩ የኢኮኖሚ እድገት ላይ እንደምትገኝ የአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ገለጹ

ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቷን ለማልማትና ለመንከባከብ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ