Back

ኢትዮጵያ በትክክለኛው የኢንዱስትሪ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የጁቡቲ ፕ/ት ገለጹ

መጋቢት 9፣ 2009

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ሊያሳድግና ሊያነቀቃ በሚችል ትክክለኛው የኢንዱስትሪ ዕድገት አቅጣጫ መከተሏን የጁቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌለህ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የሚገኙትን የጨርቃ ጨርቃና የጫማ ፋብሪካዎችን ከጎበኙ በኋላ ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው የኢንዱስትሪ አቅጣጫ ቴክኖሎጂዎችን ለማለመድና ሰፊ የሰው ሃይል ለመቅጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ወጣቶችን በተለይም ሴቶችን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸው መታዘብ መቻላቸውንና በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

የጁቡቲ ወደብ አገልግሎት ክፍያ ከሌሎች አንጻር ውድ መሆኑን ከፋብሪካዎቹ ባለቤቶች ለተነሳላቸው ጥያቄ ጉዳዮን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩበት ቃል ገብተዋል፡፡

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌለህ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎብኝተዋል፡፡

አየር መንገዱ ከዳኮታ አውሮፕላኖች በመነሳት የድሪምላይንና ኤርባስ አውሮፕላኖች ባለቤት በመሆን የአፍሪካ መሪ መሆን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር፤ እዮብ ሞጎስ


የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሁሉንም የባለድርሻ አካላት ድግፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

የባለ 5 እና 10 ብር ሞባይል ካርዶች ለክልሎች እየተሰራጩ ነው

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚዘረዝር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ወንጀለኞችን ለመለዋወጥ የተደረሰበትን ስምምነት አፀደቀች

ኤምባሲው በኬኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈታ

መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአህጉሪቱ የፀጥታ ጉዳዮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል፡- ሙሳ ፈቂህ መህመት

የመሰረተ ልማት ሂደቱን ለማቀላጠፍ ተቋማቱ በጋራ እየሰሩ ነው

ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ላይ ተስማሙ